በክልሉ ባለፉት 9 ወራት የህብረተሰቡን የአገልግሎት እርካታ ከፍ የሚያደርጉ ስራዎች መሰራታቸው ተመላከተ
የክልሉ መንግስትና የፓርቲ 9 ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በቦንጋ ከተማ እየተካኸደ ይገኛል።
Posts by Southwest Communications
የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ከኦስትሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቤይት ሜንለ-ሪዝንገርን ጋር በጽሕፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም በኢትዮጵያና ኦስትሪያ የሁለትዮሽና ባለብዙ ወገን ታሪካዊ የዲፕሎማሲና ቀጣይ የትኩረት መስኮች ላይ መክረዋል።
ውይይቱን አስመልክቶ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአውሮፓና የአሜሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር መለስ ዓለም (ዶ/ር) ኢትዮጵያና ኦስትሪያ ዘመናትን የተሻገረ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ያላቸው ሀገራት ናቸው ብለዋል
በክልሉ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በማህበራዊ ዘርፍ የህዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተከናወኑ ተስፋ ሰጪ ተግባራት ተጠናክሮ ሊቀጥሉ እንደሚገባ ተጠቆመ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የ2018 በጀት ዓመት ያለፉት 9 ወራት የመንግሥት እና የፓርቲ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
በመድረኩም በክልሉ ያለፉት 9 ወራት በተለያዩ ዘርፎች የተከናወኑ የተግባር አፈጻጸም በክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ወሰነች ቶማስ አቅርበዋል።
በክልሉ ያለውን የመሠረተ ልማት አፈጻጸም በማሳደግ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሠራ ነው
በክልሉ የ2018 በጀት ዓመት ያለፉት 9 ወራት የመንግሥት እና የፓርቲ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
የክልሉ ፀጋዎችን በአግባቡ በማልማት ኢኮኖሚ የማመንጨት አቅማቸውን ማሳደግ ላይ ትኩረት መደረጉን የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ ገለፀ።
የክልሉ መንግስትና የፓርቲ 9 ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቅርቡ አራት የሀገር ውስጥ ኤርፖርቶችን እንደሚያስመርቅ አስታወቀ፡፡
በአሁኑ ወቅት በሀገር ውስጥ 23 ኤርፖርቶች አገልግሎት እየሰጡ የሚገኝ ሲሆን፤አራት ተጨማሪ ኤርፖርቶች በቅርቡ ይመረቃሉ፡፡
እነዚህም ነጌሌ ቦረና፤ ሚዛን አማን፤ ጎሬ መቱ እና ደብረ ማርቆስ ኤርፖርት መሆናቸውን ጠቅሰው፤ አየር መንገዱ ቀጣይነት ባለው መልኩ የማስፋፊያ ሥራዎችን እየተሰራ ይገኛል
በሀገራዊ ኢኒሼቲቮች የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ተግባራት መከናወናቸውን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ገለጸ
በክልሉ ባለፉት 9 ወራት በፓርቲው መሪነት የተከናወኑ ተግባራት እየተገመገሙ ነው።
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት፦
ዛሬ ጠዋት የስራ ዘመኑን ሶስተኛ የ100 ቀናት የመንግሥት ሥራ አፈፃፀም ከዘጠኝ ወራት አጠቃላይ አፈፃፀም ጎን ለጎን መገምገም ጀምረናል።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የ2018 በጀት ዓመት ያለፉት 9 ወራት የመንግሥት እና የፓርቲ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
መድረኩ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በመንግስት እና ፓርቲ የተከናወኑ የሥራ አፈጻጸሞችን በጋራ በጥልቀት በመገምገም፣ ጠንካራ ጎኖችን ለማስቀጠልና ድክመቶችን ለማረም ያለመ ነው
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት
"ቀጣዩ የብርሃን ተስፋ!
በንፋስ ኃይል አማካኝነት ጨለማን ለመግፈፍ፣ ዐቅምን በለየ የቅድመ ጥናት እና ልዩ እቅድ ወደ ተግባር ዛሬ የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫን እውን አድርጋለች።
ይህ ፕሮጀክት 100 ሜጋ ዋት ንጹህ የኃይል አቅርቦት በመጨመር ወደ ዘርፈ ብዙ እና ቀጣይነት ባለው የኃይል መጻዒ ዕጣ ፈንታ ለመገንባት የምናደርገውን ጉዞ ያጠናክረዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሰው ኃይል ልማት ፕሮግራም ለኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ስኬት አዲስ ምዕራፍ እንደሚከፍት ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) አስታወቁ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እየተለወጠ ካለው ቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታ ጋር ራሱን እንዲያራምድ፣ዲፕሎማቶቹም በቂ እውቀትና ክህሎት እንዲኖራቸው ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ የሰው ኃይል ልማት ፕሮግራም ይፋ ማድረጊያ መርኃ ግብር አካሂዷል።
በክልሉ ላለፉት የለውጥ ዓመታት አስተማማኝ ሰላም ማስፈን የሚያስችሉ ጠንካራ የሠላምና ፀጥታ ሥራዎች ተሠርቷል:- የክልሉ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ለረጅም ጊዜ ሲጠይቁ የነበረው በክልል የመደራጀትና ፍትሐዊ የልማት ተጠቃሚነት ጥያቄን በመደመር ዕሳቤ የሚመራው የለውጡ መንግስት ምላሽ በመስጠቱ ህዳር 2014 ዓ.ም ክልሉ መመስረቱ ይታወሳል።
“ልማትን እና ብልጽግናን የሚያስብ ማንኛውም መንግሥት ከተሜነትን፣ ከተማነትን፣ ግብር መክፈልን እና አገልግሎት መስጠትን ማዕከሉ ካላደረገ ልማት ሊያመጣ አይችልም” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
“የመደመር መንግሥት ማዕከላዊ እሳቤ ስለ ሁሉ ነገር ሚዛን መጠበቅ ነው” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
“ማስቀጠል አለመኖሩ በኢትዮጵያ የሥርዓተ መንግሥት ግንባታ ውስጥ ትልቁ ስብራት መሆኑን ለይተናል፤ የትናንትናም ቢሆን ጠቃሚ ታሪክ ጠቃሚ ሥራ መጣል የለበትም፤ መደመር አለበት።” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
የዓለም የንግድ እና የኢንዱስትሪ ትሥሥር በአየር፣ በየብስ እና በባሕር ሎጂስቲክስ ስጋቶች ውስጥ መውደቁን ተከትሎ የባሕር በር ደኅንነት ጉዳይ ከምንጊዜውም በላይ አንገብጋቢ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደገለጹት፣ መንግሥት ከዓመታት በፊት የባሕር ላይ እንቅስቃሴ አደጋ ሊገጥመው እንደሚችል በመተንበይ "ከባሕር ከራቅን 130 ሚሊዮን ሕዝብ አደጋ ውስጥ ይወድቃል" የሚል የጸና አቋም ሲያራምድ ቆይቷል።
ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ የኢኮኖሚ ልብ ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ "የሉዓላዊነት ልብ" በሚል መሪ ሐሳብ ከኢቢሲ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ነው ይህንን የገለጹት።
በቆይታቸው የመደመር መንግሥት ማዕከላዊ ዕሳቤ ስለሁሉ ነገር ሚዛን መጠበቅ እንደሆነ ገልጸው÷ የሆኑ መንግሥታት አብዛኛውን ዕሳቤያቸውን ፖለቲካ ላይ አድርገው ኢኮኖሚን ተከታይ አድርገው ሞክረውታል ነገር ግን ይህ አካሄድ እምብዛም አዋጭ አልነበረም ብለዋል።
የኢትዮጵያ የኢንደስትሪ ጉዞ አዲስ ምዕራፍ እየተራመደ ይገኛል
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት የሁለት ክፍሎች ቃለምልልስ ኢትዮጵያ የአዲሱ ዘመን የኢንደስትሪ መስፋፋትን እንዴት እየበየነች እንደሆነ አብራርተዋል።
የመጀመሪያውን ክፍል ዛሬ ምሽት 2:30 ይጠብቁ።
ለተሻለ ዛሬ፣ለብሩህ ነገን ለመወሰን ካርድ ይዉሰዱ
የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ ዕለታዊ ኘሮግራሞች
ሚያዚያ 6,2018 ዓ.ም
#prosperity
በነፃ የንግድ ቀጣናዎች ውስጥ ግብዓትና ምርት ለገበያ የሚያቀርቡ ባለሀብቶች ከገቢ ግብር ነፃ እንዲሆኑ በገንዘብ ሚኒስቴር ውሳኔ ተላለፈ።
ሚኒስቴሩ ይህንን የፈቀደው የንግድ ቀጠናዎቹ ባለሀብቶችን ይበልጥ የሚስቡ እንዲሆኑ ለማድረግ መሆኑን ገልጿል።
የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ልማት በሚፈለገው መጠን እንዳያድግ ምክንያት ከሆኑት መካከል የካፒታል እጥረት፣ የግብዓት አቅርቦት ችግር እና የባለሙያ እጥረት በዋነኛነት የሚጠቀሱ መሆናቸውን ሚኒስቴሩ በመረጃው ጠቁሟል።
የአካል ጉዳተኞች በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሁሉም ሒደቶች ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግ በትብብር መስራት ይገባል አለ የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን፡፡
የፌዴሬሽኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ አባይነህ ጉጆ እንዳሉት ÷ የአካል ጉዳተኞች በቅድመ ምርጫ፣ በምርጫ ወቅትና በድህረ ምርጫ ሒደት ላይ ያላቸውን ተሳትፎ ለማጠናከር በቅንጅት መስራት ይገባል
በቅድመ ምርጫ ሒደት ላይ የአካል ገዳተኞች የምርጫ ካርድ እንዲወስዱ ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ በስፋት መከናወኑን አመልክተዋል
አሰብ ለእኛ እናታችንና ብርሃናችን ነበረች፤ ያ ታሪካዊ ቀን ሲመለስ ለማየት እንመኛለን" - የቀድሞ የአሰብ ነዋሪዎች
በአሰብ ከተማ ነግደው ያተረፉ፣ ወልደው የከበሩና ከተማዋን ያቀኑ ኢትዮጵያውያን፤ ዛሬ በኮምቦልቻ ከተማ "የአሰብ ተፈናቃዮች" በሚል መጠሪያ በራሳቸው መንደር ማህበር መስርተው ይኖራሉ።
ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ተመዝግበው ካርድዎን ወሰዱ?
ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር ጉባኤን ለማስተናገድ በሙሉ ድምፅ ተመረጠች
በስዊዘርላንድ ሉዛን በተካሄደው 88ኛው የዓለም አቀፉ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር (AIPS) ጉባኤ ላይ በተሰጠ ድምፅ ኢትዮጵያ የ2027ቱን ታላቅ መድረክ እንድታስተናግድ በሙሉ ድምፅ መመረጧን የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር በይፋ አስታውቋል።
የኢትዮጵያ የኢንደስትሪ ጉዞ አዲስ ምዕራፍ እየተራመደ ይገኛል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት የሁለት ክፍሎች ቃለምልልስ ኢትዮጵያ የአዲሱ ዘመን የኢንደስትሪ መስፋፋትን እንዴት እየበየነች እንደሆነ አብራርተዋል።
የመጀመሪያውን ክፍል ማክሰኞ ሚያዚያ 6/ 2018 ዓመተ ምህረት ከምሽቱ 2:30 ይጠብቁ።
ማዕድ ማጋራት መደጋገፍን፣ አንድነትንና መተሳሰብን የሚያጎላ መልካም እሴት ነው ሲሉ አቶ ነጋ አበራ ገለጹ
የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ በአመያ ከተማ አስተዳደር 'የቅዱስ ጳዉሎስ በጎ አድራጎት ማህበር' የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም አካሂደዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነጋ አበራ መንግሥት ሰውን ማዕከል ያደረጉ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ አስረድተዋል።
ዓለም በትኩረት ሲከታተለው የቆየው በኢስላማባድ የተካሄደው የአሜሪካ እና ኢራን የሰላም ድርድር ያለ ስምምነት መቋጨቱን የአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የልዑኩ መሪ ጄዲ ቫንስ ገልጸዋል።
ምክትል ፕሬዚዳንቱ "ከኢራን ጋር ለ21 ሰዓታት የዘለቀ ውይይት አድርገናል፤ መነጋገራችን ጥሩ ቢሆንም ስምምነት ላይ አልቻልንም" ብለዋል
ጄዲ ቫንስ በፓኪስታን አደራዳሪነት ሲካሄድ የቆየውን ውይይት ሲያብራሩ፣ ንግግሮች ነበሩ ነገር ግን ጦርነቱን በቋሚነት ለማስቆም በቂ አልነበሩም ብለዋል
ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ለትንሣኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ለትንሣኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ፕሬዝዳንቱ በመልዕክታቸው በዓሉ የሰላም፣ የጤና እና የበረከት እንዲሆን ተመኝተዋል። አክለው ገልፀዋል
በትምህርት ለትውልድ ኢንሸቲቭ ላለፉት 5 ዓመታት በክልሉ በትምህርት ዘርፍ የታዩት ተስፋ ሰጪ ውጤቶች
መንግስት ትምህርት ለሀገር ዘላቂ ዕድገት የማይተካ ሚና እንዳለውና በትምህርት ትውልድ እንደሚገነባ ፅኑ እምነት በመያዙ ትምህርት ጥራት ጉድለቶችን በተገቢው በመለየት ከመሰረቱ ለማረም የትምህርት ስልጠና ፍኖተ ካርታ ተቀርጾ ተግባራዊ በመደረጉ ውጤቶች እየተመዘገቡ መጥቷ፦ አቶ አልማው ዘውዴ